GLOBAL ACTIVITIES ETHIOPIA South Korea Ethiopia, Sidama የአለም አቀፉ የሌጀንድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን በአሜሪካ መስራች ፣ የአለም አቀፍ ፖሊስ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን በአፍሪካ ተጠሪ ፣ የኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን በአፍሪካ የበላይ ጠባቂ እና የግሎባል ትራዲሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን የአለም ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ግራንድ ማስተር ሄኖክ ግርማ በሲዳማ ክልል “ፖሊስ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን” እንዲመሰረት ከክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ ጋር ውይይት ለማድረግ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል። ዶ/ር ግራንድ ማስተር ሄኖክ ግርማ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሲደርሱ ልዩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የተከበሩ አቶ አለማየሁ ጢሞትዮስ (የሲዳማ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ) ስላደረጉልን መልካም አቀባበል ከልብ እናመሰግናለን Ethiopia, Diredewa Ethiopia, ... #ቁርሴን_ለትውልዴ! ለጋስነት ማለት የተረፈውን የሰጠ ሳይሆን ያለዉን ያካፈለ ነዉ!! ዛሬ ቁርሴን ለትዉልዴ የአለም አቀፉ ሌጀንድ ቴኳንዶ ፌድሬሽን በአሜሪካ መስራች ‘ የአለም አቀፉ ፖሊስ ቴኳንዶ ፌድሬሽን በአፍሪካ ተጠሪ ‘የኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ቴኳንዶ ፌድሬሽን በአፍሪካ የበላይ ጠባቂ እና የግሎባል ትራዲሽናል ቴኳንዶ ፌድሬሽን ም/ፕሬዚዳንት ዶክተር ግራንድ ማስተር ሄኖክ ግርማ ከህፃናቱ ጋር ቁርስ መግቦልናል አንተ የሀገር ባለ ዉለታ ከልብ እናመሰግናለን። በዚሁ #ቁርሴን ለትውልዴ! ቻሌንጅ ለመቀላቀል የምትፈልጉ ቀና ልቦች ለትውልዳችሁ እንድትቆሙ እንላለን09 161 167 0509 53 76 06 8809 46 55 63 6009 161 639 241000 326 306 316 CBE ተምሳሌት የበጎ አድራጎት ማህበር Ethiopia, Hossana Ethiopia, ሺንሽቾ የሌጀንድ GTTF/ IPTF ፌዴሬሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሺንሽቾ ከተማ በግራንድ ማስተር ሄኖክ(ዶ/ር) የተመራ ሉኡካን ቡድን የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠቱ ተገለጸ። ሺንሽቾ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ/ም (መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት):- GTTF ከማዕከላዊ ኢትዬጵያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመሆን በሺንሽቾ ከተማ በግራንድ ማስተር ሄኖክ የተመራ ሉኡካን ቡድን የአሰልጣኞች ስልጠና እና የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዕርዳታ መስጠቱን የሺንሺቾ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ገልጿል። የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንሻው ገ/ማርያም እንደገለጹት ግራንድ ማስተር(ዶክተር) ሄኖክ ግርማ የዓለም የሌጀንድ መስራች ጂቲቲፍ/ IPTF ም/ፕሬዝደንት እና የአፍሪካ የበላይ ጠባቂ መሆናቸውን ገልጸው እንደ ሺንሽቾ ከተማ የወጣቶችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የስፖርቱን መስክ ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። በስልጠናውም ወቅት 48 አሰልጣኞች እና 65 ሰልጣኞች ስልጠናውን መውሰዳቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ስፖርቱን ለማሳደግ ከመንግስት ውጭ ያሉ አካላት ወጪዎቻቸውን በመሸፈን እያገዟቸውም እንደነበረ ጽ/ቤቱ አመላክቷል። በዕለቱም ስልጠናውን ወስደው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። በመርሐ ግብሩም የሌጀድ ፕሬዝደት ዋና ፀሀፊ ቅድስት የኑቻኮ ማስተርና ቺፍ ኢንስትራክተር አላዛር ፣ ግራንድ ማስተር መኩሪያ የፊዝዮ ቴራፒ ባለሙያና አንጋፋ የውሹ አሰልጣኝ ፣ ሺያን ፲/አስር አለቃ ዘሪሁን አስፋው የGTTF በኢትዬጵያ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ስፔሻል ፎርስ አሰልጣኝ ማስተር ኢዶንያስ የአዲስ አበባ የሌጀድ ምክትል ፕሬዝደት የምርሻል አርትና የእክምና ባለሙያ ስልጠናውን በእነሱ ተከናውኗል ፣በእለቱ የከተማው አሳልጣኞች ፣ አጠቃላይ ሰልጣኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው የብልጽግና ም/ኃላፊ አቶ ሰመረ በላይነህ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኢ/በረከት ዳንኤል አቶ ታሪኩ ተስፋዬ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንዲሁም ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት አቶ ስንሻው ገ/ማሪያም የባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ምህረት ኩራቱ ተጋባዥ እንግዶች ሆንው ተገኝተዋል።